አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ ውስጥ ከጠቀመጡ ስትራቴጂያዊ የትኩረት መሥኮች አንዱ የመንግስት አደረጃጀትና አስተዳደር ሥርዓትን ማሳለጥ ነው።

ግብርና ሚኒስቴር እውቀት ላይ የተመሰረተ ሁሉን አቀፍ የሪፎርም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
በዚህም የግብርና ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች አዲስ እየተሰራ ባለው መዋቅር ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አዲሱ አረጋ የኢትዮጵያን የገጠር ትናስፎርሜሽን ትግበራን እውን ማድረግ የሚችል ተቋም ለመገንባት ሁሉን አቀፍ ሪፎርም መስራት ለነገ የማይተው ወሳኝ ተግባር መሆኑን አንስተዋል፡፡
የመደመር መንግስት የሚፈልገውን እሳቤ መሸከም የሚችል ቁመና ያለው ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እንዲቻል በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚሰራው ሪፎርም አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ለግብርና ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ ተቋማትም በሚፈለገው ልክ እንዲጠናከሩ በየተቋማቸው የቅድመ-ዝግጅት ስራዎችን እንዲሰሩ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
በውይይቱም አዲስ እየተሰራ የሚገኘው የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሪፎርም ላይ ትኩረት ያደረ ፅሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የገጠር ትራንስፎርሜሽንን እውን ለማድረግ ብሎም የዘርፉን ምርትና ምርታማነት በሚፈለገው ልክ ለማሳደግ እንዲቻል ሁሉን አቀፍ እና አካታች የሆነ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት ጠንካራ ተቋም መገንባት እንደሚገባ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል፡፡
ዘጋቢ፡- ሰለሞን ደምሰው
ፎቶ፡- ተክለመድህን አቻምየለህ
