(አዲስ አበባ፣ ጥር 4 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)
የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ ከስታርባክስ (Starbucks) ኩባንያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሮቤርቶ ቬጋ አሎንሶ ጋር የቡና ልማት እና ግብይትን በተመለከተ በኢትዮጵያ እና በስታርባክስ ኩባንያ መካከል ያለውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይታቸውም አስተማማኝ የስፔሻሊቲ ቡና አቅርቦት በማረጋገጥ የኢትዮጵያ ቡና በስታርባክስ የቡና Recipe ውስጥ መጠኑን ትርጉም ባለው ደረጃ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ በመወያየት መግባባት ላይ ተደርሷል።

በተጨማሪም የአነስተኛ አርሶአደሮች ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ ኩባንያው ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።
ስታርባክስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቁ የስፔሻለቲ ቡና ገዢ ኩባንያ ነው።
