FDRE Ministry of Agriculture

ግብርናን ማዘመን የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው!

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6/2019 (ግብርና ሚኒስቴር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም 6ኛው የጋራ ግምገማና የትግበራ ድጋፍ ተልዕኮ መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

ግብርናን ማዘመን የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጥ ለማረጋገጥ እንደሚያስችል መሠረታዊ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ተናግረዋል።

ግብርናን ለማሻሻል የሀገሪቱ የተፈጥሮና የሰው ኃይል ሀብቶችን በተቀናጀ መልኩ መጠቀም እንደሚገባም አቶ ኡስማን አስገንዝበዋል።

የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በዚህ ረገድ በሰው ኃይል፣ በክህሎት፣ በቴክኖሎጂና በመሠረተ-ልማት ያሉ ክፍተቶችን በመሙላት የግብርና ልማቱን የመቀየር ሂደት እያገዘ መሆኑንም አቶ ኡስማን አስረድተዋል።

በመድረኩ የአለም ባንክና የልማት አጋራት የስራ ሀላፊዎችን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በነገው ዕለትም በጉራጌ ዞን ቸሃና እና በስልጤ ዞን ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በሚደረግ የመስክ ምልከታ የሚቀጥል ይሆናል።