FDRE Ministry of Agriculture

የዶሮ ልማትን ወደ ዘመናዊ አሠራር እያሸጋገረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25/2018 (ግብርና ሚኒስቴር)‎ ‎በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት የተጀመረው የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የዶሮ ሥጋና እንቁላል ምርትን በማሳደግ ዘመናዊ የዶሮ እርባታን እያስፋፋ ይገኛል።

‎‎የተሻሻሉ ዝርያዎችን ማስፋፋት፣ ዘመናዊ ማባዣና ማስፈልፈያ ማዕከላትን ማጠናከር፣ የጫጩት እንክብካቤና የባዮ-ሴኩሪቲ ሥርዓትን ማሻሻል እንዲሁም የግል ባለሀብቶችን ማሳተፍ የኢኒሼቲቩ ዋና ትኩረቶች ናቸው።

‎‎በዚህም አርቢዎችን ከአነስተኛ እርባታ ወደ ገበያ ተኮርና ምርታማ የዶሮ ልማት በማሸጋገር ለምግብ ዋስትና፣ ለገቢ ምንጭ እና ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያበረክት ዘርፍ እየሆነ መምጣቱን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አመላክተዋል።