FDRE Ministry of Agriculture

የእንስሳት ልየታና ክትትል ሥርዓት በወተት ላሞችና ጥጆች ላይ ተጠናክሮ እየተተገበረ ነው

ደብረ ብርሃን፣ መስከረም 15/2019 (ግብርና ሚኒስቴር) ግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ልየታና ክትትል ሥርዓት በወተት ላሞችና ጥጆች ላይ ተግባራዊ የማድረግ ዘመቻ በአማራ ክልል፣ በሰሜን ሸዋ ዞን በተመረጡ የወተት መንደሮች እያካሄደ ይገኛል።


በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ልየታና ክትትል ስርዓት እና የእንስሳት ደህንነት ዴስክ ኃላፊ ሀድጉ መንደፍሮ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም የእንስሳት መለያ እና ክትትል ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን እና ደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን የወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ አካባቢዎች ላይ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን አስታውሰዋል፡፡


ስርዓቱን ተግባራዊ የማድረግ ዘመቻ ከሁለት ሳምንት በፊት ተጀምሮ በሸገር ከተማ፣ በኦሮሚያ ክልል አርሲ፣ ምዕራብ አርሲ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖችም በተመረጡ የወተት መንደሮች የእየተካሄደ እንደሚገኝም ዶ/ር ሀድጉ ተናግረዋል፡፡


ይህ ተግባር በወተት ላሞች ልየታና ምዝገባ ላይ የተለያዩ ተቋማትና የመስክ አካላት የሚያከናውኗቸውን ሥራዎች በአንድ ብሔራዊ ሥርዓት ለማቀናጀት እና በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የተቀመጡ የወተት ልማትና ምርታማነት ዓላማዎችን ለማሳካት የሚያግዝ ነው።
የኔዘርላንድ የልማት ድርጅት (SNV) ለዚህ ስራ ድጋፍ ማድረጉን የገለፁት ዶ/ር ሀድጉ፣ ድርጅቱ ለዘመቻ ስራው ላበረከተው አስተዋፅዖ ምስጋና አቅርበዋል፡፡


የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ተቀርፆ እየተተገበረ ላለው ስራ የእንስሳት መረጃ ስርዓቱ ወሳኝ ነው፡፡
በቀጣይም በሌሎች የወተት መንደሮች በሚገኙ በወተት ላሞችና ጥጆች እንዲሁም በሌሎች እንስሳት ላይ የመረጃ ሰርዓቱን የመተግበር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡