FDRE Ministry of Agriculture

የአፈር አሲዳማነትን እንከላከል!

የአፈር አሲዳማነት በኢትዮጵያ በተለይም ከፍተኛ ዝናብ በሚያገኙ ደጋማና እርጥበታማ አካባቢዎች የሚታይ የአፈር ለምነትን የሚጎዳ ችግር ነው። አፈሩ አሲዳማ ሲሆን እፅዋት እንደ ፎስፈረስ፣ ካልሲየም፣ ማግኒዥየምና ፖታሲየም ያሉ አስፈላጊ ንጥረ-ምግቦችን በበቂ መጠን መውሰድ አይችሉም። በተመሳሳይ ጊዜ አሉሚኒየምና ማንጋኒዝ በመጨመራቸው የእፅዋትን ሥር ከመጉዳቱም ባሻገር የሰብል እድገትንና ምርትን በእጅጉ ይቀንሳል።

በተጨማሪም በተከታታይ እርሻ፣ በአፈር መሸርሸር፣ በኦርጋኒክ ቁስ መቀነስና አሞኒየምን የያዙ የኬሚካል ማዳበሪያዎችን ያለ ተገቢው ምክረ-ሃሳብ ጠቃቀም የአፈር አሲዳማነት እንዲከሰት ያደርጋል።
በኢትዮጵያ የአፈር አሲዳማነት ችግር ኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እንዲሁም በጋምቤላ አንዳንድ እርጥበታማ አካባቢዎች በስፋት ይታያል።

የአፈር አሲዳማነት ዋና ዋና መንስኤዎች
🟤 ከፍተኛ የዝናብ መጠን በመኖሩ ካልሲየም፣ ማግኒዥየምና ፖታሲየም ከአፈር ውስጥ መታጠብ፣
🟤 አፈርን ያለማቋረጥ በሰብል ማምረት ምክንያት የንጥረ-ምግብ መሟጠጥ፣
🟤 የአፈር መሸርሸርና የላይኛው ለም ክፍል መታጠብ፣
🟤 የኦርጋኒክ ቁስ መቀነስና የሰብል ቅሪቶችን ማቃጠል፣
አሞኒየምን የያዙ የኬሚካል ማዳበሪያዎችን በተደጋጋሚና ያለ ሙያዊ ምክር መጠቀም እና የተፈጥሮ የአፈር አፈጣጠር ሂደት ይጠቀሳሉ።
የአፈራችንን ጤንነትና ለምነት ለመጠበቅ ምን ማድረግ አለብን?

📢 የማከሚያ ዘዴዎች
🟤የግብርና ኖራ መጠቀም:-
🟤የግብርና ኖራ የአፈሩን pH ከፍ በማድረግ አሲዳማነቱን ይቀንሳል፣ የአሉሚኒየምን መርዛማነት ያስወግዳል፣ የንጥረ ምግቦችንም ተደራሽነት ያሻሽላል።
🟤 ኦርጋኒክ ማዳበሪያ መጠቀም:-
ኮምፖስት፣ የከብት ፍግና አረንጓዴ ማዳበሪያዎች የአፈሩን አወቃቀር፣ ለምነትና pH መረጋጋትን ያሻሽላሉ።
🟤 የተመጣጠነ የማዳበሪያ አጠቃቀም:-
🟤የአፈር ምርመራ ውጤትን መሠረት በማድረግ ተገቢውን ዓይነትና መጠን መጠቀም የአሲዳማነትን መጨመር ይከላከላል።
🟤አሲዳማነትን የሚቋቋሙ የሰብል ዝርያዎችን መጠቀም:-
🟤እንደ አፈሩ ሁኔታ የተመረጡ ዝርያዎችን በመጠቀም የምርት መቀነስን መገደብ ይቻላል።

📢 የመከላከያ ዘዴዎች
🟤የአፈር pH በየጊዜው መመርመር፣
🟤ኮምፖስትና ሌሎች ኦርጋኒክ ማዳበሪያዎችን በቋሚነት መጨመር፣
🟤ሰብል ማፈራረቅ (Crop Rotation) እና የአፈር ሽፋን ሰብሎችን (Cover Crops) መጠቀም፣
🟤 በእርከን፣ በዕፅዋት ሽፋንና በሌሎች የአፈር ጥበቃ ዘዴዎች የአፈር መሸርሸርን መቆጣጠር፣
የሰብል ቅሪቶችን ከማቃጠል ይልቅ በአፈር ውስጥ መቀላቀል እና የኬሚካል ማዳበሪያዎችን በተመጣጠነ መጠንና በሙያዊ ምክር መሠረት መጠቀም ናቸው።
የአፈር አሲዳማነትን በጊዜው መከላከልና ማከም የአፈራችንን ጤንነትና ለምነት ይጠብቃል፣ የሰብል ምርትና ምርታማነትን ያሳድጋል እንዲሁም የቤተሰብን ገቢና የምግብ ዋስትናን ያጠናክራል።

አዘጋጅ፡- ሰለሞን ደምሰው