FDRE Ministry of Agriculture

የአደጋ ስጋት ቅነሳና አካታች የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻያ ፕሮጀክት

ውድ የገፃችን ተከታታይ ቤተሰቦቻችን፡- በዛሬው የፕሮግራም እና ፕሮጀክቶች ዝርዝር ገላጭ ፅሁፋችን የአደጋ ስጋት ቅነሳና አካታች የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻያ ፕሮጀክት/De-Risking Inclusion and Value Enhancement of Pastoralist Economies (DRIVE) ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡

የአደጋ ስጋት ቅነሳና አካታች የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻያ ፕሮጀክት በምሥራቅ አፍሪካ አገሮች (ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ) የአርብቶ አደሮችን ኑሮ ለማሻሻልና የድርቅ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ እየተተገበረ ያለ ፕሮጀክት ነው።

ፕሮጀክቱ ከ2015 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ከዓለም ባንክ በተገኘ የ115 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በኢትዮጵያ አምስት ክልሎች (ኦሮሚያ፣ ሶማሊ፣ አፋር፣ ደቡብ ኢትዮጵያና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ) በ187 ወረዳዎች እየተተገበረ ይገኛል።

ይህ ፕሮጀክት ሁለት አብይት ምሰሶዎች ያሉት ሲሆን 1ኛው በአርብቶአደሩ አካባቢ የድርቅ አደጋ ስጋት መቀነስና አካታች የሆነ የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻል ሲሆን 2ኛው ደግሞ የእንስሳት ልማት እሴት ሰንሰለት እና የግብይት ሥርዓት ማጠናከር ነው።

የአደጋ ስጋት ቅነሳና አካታች የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻያ ፕሮጀክት በእንስሳት ኢንሹራንስ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የቁም እንስሳት ማቆያ ማዕከላት ግንባታና የንግድ ተደራሽነት በማሳለጥ የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነትና ዘላቂ አቅም ለማረጋገጥ እየሰራ ነው።

ይህም በአርብቶአደር አካባቢዎች የእንስሳት ሀብቱ በድርቅ እንዳይጎዳ በማድረግ የእንስሳት ኢንሹራንስና የብድር አገልግሎት በማመቻቸት፣ የምግብ ዋስትናና የገቢ ምንጭ በማሳደግ ረገድ ጅምር ውጤቶች ተገኝተዋል።

ፕሮጀክቱ ባከናወናቸው ተግባራት የእንስሳት ኢንሹራንስ በመመዝገብ እና ቅድመክፍያ በመክፈል ፕሮጀክቱ ከጀመረበት አንስቶ ባሳለፋቸው ምዝገባ ጊያያት ወደ 200 ሺ አርብቶአደሮች ተጠቃሚ ሲሆኑ ከ47 ሺ በላይ አ/አደሮች ኢንሹራንስ ተቀብለው ለእንስሳቱ ውሃ፣ መኖና መድሀኒት በመግዛት ተጠቃሚ አድርገጓል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ 7 ሁሉን ያሟላ የእንስሳት ማቆያ ማዕከል፣ የእንስሳት ሕክምናና ጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣ የእንስሳት ጤና ምርመራ ማዕከል እንዲሁም የኳራንታይን፣ የገበያ መሰረተ ልማት ማዕከላት ግንባታ እና እድሳት ዘርፈ ብዙ ውጤቶች ያስመዘገበ ሲሆን በእንስሳት ግብይት ቀጠናዊና ዓለማቀፋዊ ትሥሥር በመፍጠር ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

የአደጋ ስጋት ቅነሳና አካታች የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻያ ፕሮጀክት በአርብቶአደር አካባቢ የተሻሻለ የእንስሳት ልማት፣ የኢኮኖሚ አካታችነትና ጠንካራ የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ ከዚህ የበለጠ ለውጥ ያስመዘግባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#ከማምረትበላይ

#BeyondProduction