FDRE Ministry of Agriculture

የአርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት ሀገራዊ የጋራ ጥምረት መድረክ ምስረታ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) የአርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት ሀገራዊ የጋራ ጥምረት መድረክ (National Farmer Field School Platform) ምስረታ የፌደራል፣ የክልሎች እና የአጋር አካላት ተወካዮች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

የግብርና ኤክስቴንሽን ስርዓት በማጠናከር የአገልግሎት ተደራሽነት ለማሳለጥና የአርሶ አደሩን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለማሳደግ በተለያዩ አካላት ሲካሄድ የነበረውን የአርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት አተገባበር ወጥነት የሚያመጣ የተዋናኞችና የባለድርሻ አካላት ሀገራዊ የጋራ ጥምረት በዛሬው እለት ተመስርቷል፡፡

በምስረታ መድረኩ የአርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት ሀገራዊ የጋራ ጥምረት መድረክ የባለድርሻ አካላት የግንኙነት ሁኔታ፣ የመተዳደሪያ ደንብ እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

ግብርና ሚኒስቴር ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ሆርቲ ላይፍ ፕሮጀክት፣ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ላይቭስቶክ ፕሮጀክት፣ ተሳትፎዓዊ የግብርናና የአየር ንብረት ሽግግር ፕሮግራም፣ ከጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ፣ ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት እንዲሁም WEGO/Women’s Empowerment through Gender Transformative Market Opportunities Project/ ለአርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት ሀገራዊ የጋራ ጥምረት መድረክ ምስረታ ጉልህ አስተዋፅዖ አበርክተዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ዮሐንስ ደመቀ

ፎቶ፦ ጌታቸው ምትኩ