FDRE Ministry of Agriculture

የአረንጓዴ አሻራ የ5 ዓመታት የስኬት ጉዞ!

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የተፈጥሮ ሃብት መመናመንና የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን ዓሉታዊ ተፅዕኖን በመከላከል የግብርናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ብሎም ዘላቂነት ያለው አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት እንዲቻል የተፈጥሮ ሃብትን መጠበቅና በዘላቂነት መንከባብ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው፡፡

በአንድ ወቅት ከ40 በመቶ በላይ የደን ሽፋን እንደነበራት ይነገርላት የነበረችው ኢትዮጵያ በወቅቱ በነበረው ዘላቂ ያልሆነ የተፈጥሮ ሃብትና የመሬት አጠቃቀም ምክንያት የደን ሽፋናችን ወደ 3 በመቶ ወርዶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡

በ2011 ዓ.ም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሀሳብ አመንጭነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ የአካባቢን ተፈጥሯዊ ገፅታ በመጠበቅና በመንከባከብ የደን መመናመንና የአፈር መሸርሸርን ከመከላከል ባሻገር የሃገሪቱን የደንና የአረንጓዴ ሽፋን በማሳደግ ንፁህ አየርና ውሃ እንዲኖር አድርጓል፤ ለበርካታ ዜጎችም የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡

በዚህም በ2013 ዓ.ም 6 ነጥብ 8 ቢሊዮን፣ በ2014 ዓ.ም 7 ነጥብ 2 ቢሊዮን፣ በ2015 ዓ.ም 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን፣ 2016 ዓ.ም 7 ነጥብ 5 እንዲሁም በ2017 ዓ.ም 8 ቢሊዮን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን በ2018 ዓ.ም 8.5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዷል፡፡

በአጠቃላይ በአንደኛውና በሁለተኛው ምዕራፍ የተተከሉ ችግኞችን 50 ቢሊዮን ለማድርስ ግብ የታጣለ ሲሆን ይህም ተግባር ሀገራችን በአለም ትልቁ ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት ልማት መርሃ-ግብር የሚተገበርባት ሀገር እንድትሆን ከማስቻሉም በላይ የደን ሽፋን መጠንን ወደ 23.6 በመቶ እና ከዛ በላይ እድገት እንዲመዘገብ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል፡፡