ሰመራ፣ መስከረም 11/2019 (ግብርና ሚኒስቴር) ሁለተኛ ቀኑን የያዘው 2ኛው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ መካሄዱ የቀጠለ ሲሆን ፌስቲቫሉን አስመልክቶ በቴምር ልማት፣ ምርትና ምርታማነት ዕድገት፣ በገበያ ትስስርና ኢንቨስትመንት ዕድሎች እንዲሁም በቴምር ልማት ምርምር ዙሪያ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የ“Khalifa International Award for Date Palm and Agricultural Innovation” ዋና ጸሃፊ አብደልወሃብ አልቡካሪ ዛይድ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ፌስቲቫሉ ልምድና ተሞክሮ የሚቀሰምበት መሆኑን ገልጸው፣ በአፋር ክልል ለቴምር ልማት ያለውን አቅም በአግባቡ በመጠቀም ምርታማነቱን ለማሳደግ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመድረኩም የኢትዮጵያን የቴምር ምርትና ምርታማነትን አቅም ማጎልበት፣ በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች እንዲሁም ዕድሎች እና ስልቶች ላይ ያተኮረ ጽሁፍ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድሪባ ገለቲ ናቸው።

የቴምር ልማት ለምግብና ለገቢ ምንጭነት ከሚኖረው አስተዋጽኦ ባሻገር በግብርናው ዘርፍ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ አቅም እንዳለው ዶ/ር ድሪባ ገለቲ ባቀረቡት ጽሁፍ አብራርተዋል።
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ፍሬው መክብብ የኢትዮጵያ ቴምር ልማት የ10 መሪ ዕቅድ ላይ ትኩረት ያደረግ ጽሁፍ ባቀረቡበት ወቅት በሃገራችን በሞቃታማ አየር ንብረት ባላቸው አካባቢዎች በተለይም በአፋር ክልል የቴምር ልማትን ለማስፋፋት ሰፊ አቅም እንዳለ አብራርተዋል።

