FDRE Ministry of Agriculture

የስርዓተ-ምግብ ተኮር ግብርና ለአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት ዕድገት ወሳኝ ነው


የሥርዓተ-ምግብ መጓደል በቂ የምግብ አቅርቦትና ተደራሽነትን ያለማረጋገጥ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ስለሚመረተው ምግብ የንጥረ ምግብ ይዘትና የስብጥር ሁኔታ እንዲሁም የቤት ውስጥ አመጋገብንም ይጨምራል።


በኦሮሚያ ክልል በተመረጡ ቀበሌዎች አርሶአደሮች በጓሯቸው የሚያመርቱትን የምርት አይነት ከስርዓተ-ምግብ ተኮር አንጻር እንዲያለሙ እየተሰራ ነው፡፡


በአርሶአደሮች ዘንድ ግንዛቤ በመፈጠሩ በጓሮዋቸው ሰብሎችን አምርተው በመጠቀም የአመጋገብ ስርዓተቻው እየተቀየረ ነው፡፡


ለዚህ ውጤት መመዝገብ የስርዓተ-ምግብ ተኮር ግብርና ሞዴል መንደር መመስረት አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን በምዕራብ አርሲ ዞን የስርዓተ-ምግብ ተኮር ግብርና እና የአቅም ግንባታ ባለሙያ አቶ አንበሴ ጀና ተናግረዋል፡፡


ምዕራብ አርሲ ዞን በሻሸመኔ ወረዳ የተርፌ ወተሬ ቀበሌ ነዋሪ አርሶአደር ከድር ኤለሞ የስርዓተ-ምግብ ተኮር ስልጠና በመውሰዳቸው እንደቤተሰብ የአመጋገብ ስርዓታቸው እየተቀየረ ይገኛል፡፡


በፊት ምርቱ ቢኖርም አጠቃቀሙን ባለማወቃቸው በቀን ውስጥ አሰባጥረው አይመገቡም ነበር፡፡ አሁን ግን ከአርሶአደር ማሰልጠኛ ማዕከል በተሰጣቸው የስርዓተ-ምግብ ተኮር ስልጠና ግንዛቤ በማግኘት በጓሮአቸው የተለያዩ የአትክልትና የፍራፍሬ ዐይነቶችን በማልማት አሰባጥረው ይመገባሉ፡፡


አርሶአደሮቹ የስርዓተ-ምግብ ተኮር አሰራርን በመከተል ምግባቸውን በቤታቸው አሰባጥረው በማዘጋጀት መመገብ ከጀመሩ ወዲህ የቤተሰባቸው ጤና ከመጠበቁም ባሻገር ከቤተሰብ ፍጆታ የተረፈውን ምርት በመሸጥ ጥሩ ገቢ እያገኙ ነው፡፡


ጤናማና ምርታማ ማህበረሰብ ለመፈጠር የሰርዓተ-ምግብ ተኮር ስልጠናን ማስፋት ለግብርናው ምርትና ምርታማነት ወሳኝ በመሆኑ በሁሉም የሀገሪቱ አከባቢዎች መስፋት አለበት፡፡


ዘጋቢ፡- ካሳሁን ማለቶ
ፎቶግራፍ፡-ያሬድ አሰፋ

#ከማምረትበላይ
#BeyondProduction