አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) እንደ ሀገር የግብርናውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር በሰብል ልማት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ቁፋ ሙስጠፋ (ዶ/ር) በዘንድሮ መኸር ወቅት አርሶ አደሮች ስንዴ፣ ቦሎቄና ሌሎች ሰብሎችን እያለሙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ስንዴ በኩታ-ገጠም 14‚400 ሄ/ር መሬት እየለማ ሲሆን በቦሎቄ ደግሞ 5 ሺህ ሄ/ር መሬት መሸፈኑን ገልጸዋል፡፡
በክረምቱ ወቅት የተዘራው አዝመራ የሰብል ጥበቃ፣ ክትትልና እንክብካቤ እየተደረገለት በመሆኑ ሰብሉ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ኃላፊው አያይዘው ተናግረዋል፡፡

በዚህም ገበያ ተኮር ሰብሎች ላይ ትኩረት በመሰጠት አርሶ አደሩን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
አርሶ አደር እሬሶ ቡኒሶ በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደ በቦቴ ፊሊቻ ወረዳ ስንዴን በ151 ሄ/ር መሬት ላይ በክላስተር ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር እያለሙ ሲሆን በዘንድሮው አመት ጥሩ ምርት እንጠብቃለን ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ በአካባቢው የቦሎቄ ምርትም በ100 ሄ/ር መሬት ላይ በክላስተር እየለማ ይገኛል፡፡
ዘጋቢ፡- ካሳሁን ማለቶ
ፎቶ፡- ማቲዎስ ተገኝ
