ሐረር፣ ሚያዝያ 30/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ግብርና ሚኒስቴር ከሐረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ ጋር በመቀናጀት የተዘጋጀ የስትራቴጂ ትውውቅና የምግብ ዓውደ ርዕይ የተካሄደ ሲሆን በዝግጅቱም ከሐረሪ ክልል እና ከድሬዳዋ አስተዳደር የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የሐረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ ነስረዲን አሕመድ እንደተናገሩት ባለፉት ሶስት ዓመታት በክልል ደረጃ ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ስርዓትን ለማሻሻል በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።

በግብርና ሚኒስቴር የምግብና ሥርዓተ ምግብ ፅ/ቤት አስተባባሪ ወ/ሮ አለምፀሃይ ስርጋዊ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ በተመለከተ ባቀረቡት ፅሁፍ፤ አምራች የሆነ ዜጋን ለመፍጠር ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ስርዓትን በማስወገድ የህፃናትን የዕድገት ሁኔታ ማሻሻል ይገባል ብለዋል።

በመድረኩም የድህረ-ምርት አያያዝ፣ የምግብ ደህንነትና ጥራት ስትራቴጂ እንዲሁም ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ ላይ ትኩረት ያደረጉ ፅሁፎች እንዲሁም የሐረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ የምግብና ሥርዓተ ምግብ የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመጨረሻም የክልሉ ም/ፕሬዝዳንት እና የግብርና ቢሮ ሃላፊ ሮዛ ዑመር በተገኙበት በሐረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ የምግብ አውደ-ርዕይ እና በገጠር ኮሪደር የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ተጎብኝቷል።

ዘጋቢ፦ ሰለሞን ደምሰው
ፎቶ፦ ዮዲት እንዳለው
