FDRE Ministry of Agriculture

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በተግባር ያገዘው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር


የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ነው፡፡

ባለፉት ሰባት ዓመታት ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን 40 በመቶ የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ ናቸው፡፡

መርኃ-ግብሩ የከርሰ ምድር የውሃ አቅምን በማጎልበት የመስኖ እርሻዎች እንዲስፋፉ ሚናውን እየተወጣ ከመሆኑም ባሻገር የደን ሽፋንን በማሳደግም ትልቅ አበርክቶ አድርጓል፡፡

አረንጓዴ አሻራ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስና የአፈር ለምነትን በመጨመር የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት እንዲሻሻል አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ባለፉት ዓመታት ለምግብነት አገልግሎት የሚውሉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ጨምሮ ሌሎች ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በስፋት የተተከሉ ሲሆን በእነዚህም ለህብረተሰቡ የገቢ ምንጭና ለሥርዓተ-ምግብ መሻሻል የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ጉልህ ድርሻ እያበረከተ ይገኛል፡፡

በመርኃ-ግብሩ የተተከሉ ችግኞች የደን ሽፋንን ከማሳደግ ጎን ለጎን ለማር ምርት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ወጣቶችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች በመደራጀት የንብ ማነብ ስራ ላይ በመሰማራት የማር ምርት በማምረት ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ ነው፡፡

ከዚህም ጋር በተያያዘ በበርካታ ዘርፎች ሰፊ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር በተለይም የወጣቶችንና የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እያሳደገም ይገኛል፡፡

መርኃ-ግብሩ ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑና የተራቆቱ አካባቢዎች ወደ ምርታማነት እንዲለወጡ በማድረግ ለምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ የራሱን አስተዋጾኦ እያበረከተ ሲሆን በቀጣይም በአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ለመትከል የታቀደውን ችግኝ በመትከል በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት የሚያሳልጥ ይሆናል፡፡

እንዲሁም መርኃ-ግብሩ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ለሀገራችን ተጨማሪ አቅም እየፈጠረ ሲሆን ኢትዮጵያ በመርኃ-ግብሩ ያሳየችው ልምድና ስኬት ተሰሚነቷን በይበልጥ የሚያሳድግና ይህንን ውጤታማ ልምድ ለሌሎች ሀገራት በማካፈልም ወዳጅነትን በይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ አቅም ይፈጥራል፡፡

አዘጋጅ፡- ሰለሞን ደምሰው

#ከማምረትበላይ
#BeyondProduction