FDRE Ministry of Agriculture

የሌማት ትሩፋት በአማራ ክልል በደብረብርሃን ከተማ

(አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)

በደብረብርሃን ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የወተትና የእንቁላል ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

በከተማውና አካባቢው የገጠር ቀበሌዎች አርሶ አደሮችን በወተት ልማት ዘርፍ አደራጅቶ ውጤታማ ለማድረግ በበጋ ወቅት የተሰሩ የተፋሰስ ልማቶችን በእንስሳቱ መኖ በመሸፈን እንዲጠቀሙ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ታሪኳ እሸቱ አስረድተዋል።

የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብሩን ውጤታማ ለማድረግ የክትትልና ድጋፍ ስራ በማጠናከሩ ባለፈው ዓመት የነበረን በቀን ከ100 ሺህ ሊትር የወተት ምርት በዚህ ዓመት ወደ 120 ሺህ ሊትር በላይ ማሳደግ መቻሉን ጠቅሰዋል።

የወተት ምርታማነትን ለማሳደግም የእንስሳቱን ጤና መጠበቅና የመኖ አቅርቦት ላይ ትኩረት መሰጠቱን እንዲሁም የወተት ምርቱን ከአርሶ አደሩ በመሰብሰብ እሴት ለመጨመር ለገበያ ለማቅረብ አራት ፋብሪካዎችና 17 አነስተኛ አቀነባባሪዎች እንዲሰማሩ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

የወተት ምርቱ ማደግም የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚ ከማሳደግ ባለፈ በወተት፣ በእረጎ፣ በችዝ፣ ለከተማው ሕዝብና ለአዲስ አበባ ገበያ እየቀረበ ይገኛል።

የእንቁላል ምርታማነትን በማሳደግ አሁን ላይ ተደራጅተው በሚንቀሰቀሱ ነዋሪዎች በቀን 125 ሺህ እንቁላል በማምረት ለገበያ እየቀረበ መሆኑ አመልክተዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

#ከማምረትበላይ
#BeyondProduction