(አዲስ አበባ፣ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)
“የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ፣ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ እና የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽነር ልዕልቲ ግደይን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በሲምፖዚየሙ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። የሲምፖዚየሙ አካል የሆነ የህብረት ስራ አውደ ርዕይና ባዛርም ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚካሄድ ተገልጿል።
እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በሚቆየው አውደ ርዕይና ባዛር ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ ህብረት ስራ ማህበራት እንደሚሳተፉ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡