FDRE Ministry of Agriculture

የሃገራችንን የጥጥ ምርት ተወዳዳሪ ማድረግ የሚያስችል ሰነድ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ግብርና ሚኒስቴር የሃገራችንን የጥጥ ምርት ተወዳዳሪ ለማድረግ የተዘጋጀ የጥጥ ምርት ጥራት አጠባበቅና ቁጥጥር ረቂቅ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የጥጥ ማምረት አቅም እጥረት ሳይሆን በግብርናና ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ተቋማት መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ክፍተት ነው ብለዋል፡፡

የጥጥ ምርት ጥራት አጠባበቅና ቁጥጥር ስርዓት ለጥጥ ምርት ከማሳ እስከ ኢንዱስትሪ አቀርቦት ድረስ ያለውን ዓለምአቀፋዊ ተሞክሮዎችን መሰረት ያደረገና ለገበያ ትስስር መደላድልን የሚፈጥር ነው።

የጥጥ ምርት ጥራት አጠባበቅና ቁጥጥር ስርዓት እንደ ሃገር በጥጥ ምርት ጥራት ተወዳዳሪ ለመሆንና ህጋዊ ምዕቀፍን ተከትሎ ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ በቡና ላይ የታየውን ተሞክሮ ወደ ጥጥ ለማምጣት ያሰበ ስራ መሆኑም በውይይቱ ተመላክቷል፡፡

የጥጥ ምርት ጥራት አቅርቦትና ደረጃ መስጠት የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ከዘር እስከ ማዳመጫ ያለውን ስርዓት እንዲቆጣጠርና የላብራቶሪ ናሙናዎችን የሚያጠራ ተቋም እንዲሆንም በጥናቱ ተለይቶ ተቀምጧል፡፡

በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ የተሳታፊዎችን ገንቢ ሃሳብ በማካተት ሰነዱ ጸድቆ ወደ ትግበራ የሚገባ ሲሆን በውይይቱም ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ባለድርሻ አካለት፣ እንዲሁም የጥጥ አምራቾችና የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ተሳትፈዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ራቢያ ፋንታው

ፎቶ፡- ዮዲት እንዳለው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *