FDRE Ministry of Agriculture

ከ740 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በቦንጋ ከተማ የተገነባው የግብርና ማዕከል ተመረቀ

(አዲስ አበባ፣ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ ከ740 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል ተመርቋል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቀጠና ግብርናን ለማዘመን ታስቦ በቦንጋ የተገነባው የተቀናጀ የግብርና ግብዓትና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቆ ተከፍቷል።

በቦንጋ ከተማ በ743 ሚሊዮን ብር ወጪ በ2.5 ሄክታር መሬት ላይ ያስገነባው ማዕከሉ፤ በውስጡ ባለ አራት ወለል የአስተዳደር ህንጻ፣ በዓመት ከ150 ሺህ ኩንታል በላይ ዘር ማዘጋጀት የሚያስችል ዘመናዊ የዘር ማበጠሪያ ማሽን፣ የግብርና ግብዓት ማከማቻ መጋዘኖች፣የእርሻ መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂ ማሳያ እንዲሁም ዘመናዊ የዘር ቁጥጥር ላብራቶሪን ያካተተ መሆኑን መሆኑ ተጠቅሷል።

ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ከፍት የሆነው ማዕከሉ በዋናነት ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ ከፊል ኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች ተደራሽ ይሆናል ተብሏል።

ማዕከሉ የተሟላ የዘርና ግብርና ግብዓት አቅርቦት፤ የአፈር ማዳበሪያና ፀረ ተባይ ኬሚካል አቅርቦት፤ የእንሳሳት መድኃኒት አቅርቦት፣ የተፈጥሮና ኬሚካል ማዳበሪያ እንዲሁም የእርሻ የሜካናይዜሽን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

ከማምረትበላይ

Beyond Production

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *