FDRE Ministry of Agriculture

እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!

ከጳጉሜ ቀናት አከባበር መርሐ-ግብሮች አንዱ የሆነው “የእመርታ ቀን” ዛሬ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም “እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሠራራት!” በሚል መሪ ቃል በኢኮኖሚ ዘርፍ ተቋማት አዘጋጅነት በግብርና ሚኒስቴር የኮንፈረንስ ማዕከል በመካሔድ ላይ ይገኛል፡፡

መርሐ-ግብሩን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በክብር እንግድነት ተገኝተው ያስጀመሩት ሲሆን በመቀጠልም “እምርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡