FDRE Ministry of Agriculture

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ያሳየችው ስኬት እንደ አርአያነት የሚወሰድ ነው- የላይቤሪያ መንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች

ቢሾፍቱ፣ ሚያዝያ 7/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) የላይቤሪያ መንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ ጋር በመሆን ኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ እያደረገች ያለችውን ጥረትና በዚህም እስካሁን የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ ተሞክሮ ለመለዋወጥ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ አካባቢ የመስክ ጉብኝት አደረጉ።

ኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በዚሁ ወቅት ተናግረዋል፡፡

በዚህም ተግባር በዘርፉ በርካታ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ የላይቤሪያ መንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችም ኢትዮጵያ በዘርፉ እያከያከናወነች ያለችው ስራ አበረታች መሆኑን ያዩበት ጉብኝት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በግብርና ልማት ዘርፍ ላይ ያላቸውን ትብብር ወደ ፊት አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ በትኩረት ለመስራት የሚያስችል መግባባት መፈጠሩንም ጠቁመዋል።

የላይቤሪያ መንግስት ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ሳሙኤል ኮፊ ውድስ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ላይ ያሳየችው ስኬት እንዲሁም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የምታደርገው እንቅስቃሴ እንደ አርአያነት የሚወሰድ መሆኑን አብራርተዋል።

በመስክ ጉብኝቱም ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ውስጥ ምርት ለመተካት፣ የኤክስፖርት ምርቶችን ለማሳደግ እንዲሁም ከስራ ዕድል ፈጠራ አኳያ በግብርናው ሴክተር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተምሳሌታዊ መሆናቸውን የልዑካን ቡድኑ አባላት በጉብኝታቸው ወቅት ገልፀዋል።

ዘጋቢ፡- ሰለሞን ደምሰው
ፎቶ፡- ተክለመድህን አቻምየለህ

#ከማምረትበላይ #BeyondProduction