FDRE Ministry of Agriculture

አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶአደሮች በማላመድ ላይ እየሰራ የሚገኘው ጆይቴክ ፋርም

በሀገራችን በግብርናው ዘርፍ የልማት መስክ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተለያዩ ምርቶችን ለሃገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እያቀረቡ ይገኛሉ።


ለአብነትም ጆይቴክ ፋርም በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ዘርፉን የሚያዘምኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በማከናወን ዘመናዊ ግብርናን ዕውን እያደረገ ይገኛል።

ጆይቴክ ፋርም በዘመናዊ ላቦራቶሪዎች በመታገዝ እፀዋትን ያለአፈር የማሳደግ ቴክኖሎጂ (Hydroponic) በመተግበር የአትክልት፣ የፍራፍሬና የቅመማቅመም ምርቶችን በማምረት ላይ ይገኛል።

ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ የአትክልት እና ፍራፍሬ ችግኞችን በዚሁ ቴክኖሎጂ በመታገዝና በማፍላት ለአርሶአደሮች በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ በማድረግ እንዲሁም አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶአደሮች በማላመድ የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት ለማሳደግ የበኩልን አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው፡፡

ጆይቴክ ፋርም የሚያመርታቸውን ምርቶች ለሀገር ውስጥ ገበያ ከማቅረብ ባለፈ ወደ ተለያዩ የዓለም ገበያዎች በመላክ ላይ ይገኛል።

ይህም ፋርም ለ1 ሺህ 400 ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 75 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

አዘጋጅ፡- ሰለሞን ደምሰው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *