FDRE Ministry of Agriculture

አካታች እና ዘላቂ የግብርና እሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮጀክት

የአካታች እና ዘላቂ የግብርና እሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮጀክት/Inclusive and Sustainable Agricultural Value Chains Development Project (ISVCDP) ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡

ፕሮጀክቱ የዳቦ እና የማካሮኒ ስንዴ፣ የፋብሪካ ቲማቲም፣ አቮካዶ እና አናናስ የሚያመርቱ አርሶ አደሮችን ከሁለት አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጋር ማለትም በኦሮሚያ ከሚገኘው ከቡልቡላ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በሲዳማ ክልል ይርጋለም ከተማ ከሚገኘው የይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የግብርና ምርት ከሚያቀነባብሩ ፋብሪካዎች ጋር እያስተሳሰረ ይገኛል፡፡

የተመረጡ የግብርና ምርቶችን የሚያቀነባብሩ ፋብሪካዎች የግብርና ግብዓት እጥረት እንዳይገጥማቸው እንዲሁም ለአርሶ አደሩ ቀልጣፋና ዘላቂ ገበያ እንዲፈጠር ፕሮጀክቱ ባለው አቅም እና ተደራሽነት እየሰራ ይገኛል፡፡

ለአርሶ አደሩ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት፣ የመሠረተ ልማት ግንባታ በማካሄድ፣ የስራ ዕድል ፈጠራ እና ፋይናንስ እና የብድር አቅርቦትን በማመቻቸት፣ የሴቶች እና ወጣቶችን አቅም ማጎልበት፣ ስርዓተ ምግብ-ተኮር ግብርናን በማስተዋወቅ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ፕሮጀክቱ በዕቅድ ላይ የተመሠረተ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

ፕሮጀክቱ ከ 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እየተተገበረ ሲሆን ፕሮጀክቱን በገንዘብ (የረዥም ጊዜ ብድር በማቅረብ) በ30 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ በጣሊያን መንግስት በጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ እየተተገበረ ይገኛል፡፡

ፕሮጀክቱ የእህል ማሰባሰቢያ መጋዘኖች በመገንባት፣ የገበያ ማዕከላት ግንባታ እንዲሁም የተለያዩ የግብርና ማሽነሪዎችን ለወጣቶች እና የህብረት ስራ ማህበራት ግዥና ስርጭትን ጨምሮ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በኦሮሚያ፣ ሲዳማ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በ49 ወረዳዎችን እየተተገበረ የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት ወደ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሚጠጉ ቀጥተኛ ያልሆኑ ተጠቃሚዎች እንዲሁም 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ቀጥተኛ ተጠቃሚዎችን ተደራሽ ያደርጋል።

ፕሮጀክቱ አምራች አርሶ አደሮችን፣ ድርጅቶችን፣ የግብርና ምርምር ማዕከላትን፣ አነስተኛ አገልግሎት ሰጪዎችን፣ የግብርና ምርት አቀነባባሪዎችን፣ ነጋዴዎችን እና ሴቶችን ጨምሮ በግብርና እሴት ሰንሰለት ውስጥ ያሉ ተጠቃሚዎችን እና አጋሮችን በእሴት ሰንሰለቱ ተገበውን ሚና አንዲጫወቱ በመደገፍ ላይ ይገኘኛል።

ቀልጣፋና ቀጣይነት ያለው የአመራረት ስርዓት እንዲጠናከር እንዲሁም የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ ከሆኑት አግሮ ኢንዱስትሪዎች ጋር የገበያ ትስስር መፍጠር እና የህብረት ስራ ማህበራትን ሚና ማጎልበት እና አርሶ አደሩ የሚገባውን ጥቅም ከእሴት ሰንሰለቱ እንዲያገኝ ፕሮጀክቱ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡