FDRE Ministry of Agriculture

ትልቁ እህል ቦርቧሪ ተባይ ምንድን ነው?     

ድህረ-ምርት ብክነት (post-harvest loss) ማለት ማንኛውም የሰብል ምርት ተመርቶ ለመሰብሰብ ከደረሰበት ጊዚ አንስቶ ወደ ተጠቃሚው ደርሶ ጥቅም ላይ እስከሚዉልበት ድረስ ያሉትን የሰብል ምርትን በብዛት እና በጥራት የመቀነስን. ሂደቶች የሚያጠቃልል ፅንሰ ሀሳብ ነው። በነዚህ ሂደቶች ውስጥ ደግሞ ለብክነት ቁልፍ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል ከፍተኛውን ዋጋ የያዙት የጎተራ ተባዮች ናቸው፡፡ በተለይም በባህላዊ ማከማቻ ሁኔታዎች ውስጥ የእህል መጠንና ጥራት በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ፣ የተከማቸ ምርት እንዲበከል እና የገበያ እና የዘር ዋጋ እንዲጠፋ ምክንያት ከሆኑት መካከል የጎተራ ነፍሳት ተባዮች እንደ ዋነኛ የጥፋቱ ምክንያት ይጠቀሳሉ።

በአሁኑ ጊዜ ከእነዚህ የጎተራ ነፍሳት ተባዮች መካከል ትልቁ እህል ቦርቧሪ (Greater Grain Borer) በኢትዮጵያ ውስጥ የተከማቸ በቆሎ እና የደረቀ ካሳቫን ከሚጎዱ በጣም አጥፊ ነፍሳት ተባይ አንዱ ነው። ጎልማሶችም ሆኑ እጮች ወደ ተፈለፈሉ የበቆሎ እህሎች (shelled maize grains)፣ ያልተፈለፈሉ ግን የተሸለቀቁ የበቆሎ ጆሮዎች (dehusked but unshelled ears)፣ ያልተሸለቀቁ የበቆሎ ኮቦች ከነቅርፊት (intact cobs with husk) እና የካሳቫ ቺፕስ ቦርቡረው የመግባት አቅም አላቸው፡፡ 

በመሆኑም በማከማቻ ጊዜ ምንም የመከላከያ ወይም መቆጣጠሪያ ዘዴ ካልተደረገ በበቆሎም ይሁን በካሳቫ ምርት ላይ እስከ 100% የሚደርስ የምርት ብክነት የሚያስከትል ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ምርቱን የማበላሸት፣ የገበያ ዋጋ መቀነስ ወይም በገዢው ተቀባይነት አለማግኘትን ያስከትላል፡፡ ይህ ተባይ ከበቆሎ እና ከካሳቫ ሌላ በእንጨት እንዲሁም በባህላዊ የማከማቻ መዋቅሮች ውስጥ የመቆየት ከፍተኛ አቅም ያለው ሲሆን ጥቃቱም ከመስክ ጀምሮ እስከ ማከማቻ ድረስ የሚቀጥል በመሆኑ ቁጥጥሩን አስቸጋሪ ያደርገዋል።

ሙሉውን ፅሑፍ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://www.moa.gov.et/wp-content/uploads/2026/03/Borbari.docx