FDRE Ministry of Agriculture

ተስፋ ሰጭ የትብብር ስራ ለእንስሳት በሽታ ምርመራና ምርምር

ኢትዮጵያ ሰፊና አይነተ ብዙ የእንስሳት ሃብት እንዲሁም ምቹ ስነ-ምህዳር ያላት አገር ስትሆን ከዘርፉ ተገቢውን ጥቅም ለማግኘት ሰፊ ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች፡፡ አገሪቱ ካላት አይነተ ብዙ እንስሳት መካከል በተለይም በአርብቶና ከፊል አርብቶ አደሩ አካባቢ የግመል ሃብት ተጠቃሽ ነው፡፡

ይህን ትልቅ ሃብት በተገቢው መንገድ ለመጠቀም የእንስሳት ጤና አገልግሎት ዋነኛው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ግመሎችን የሚያጠቃውን ያልታወቀ የግመሎች በሽታን በዘላቂነት መፍታት እንዲቻል በትብብር መስራት ያስፈልጋል፡፡ ያልታወቀ የግመል በሽታ በተለያዩ ግመል አርብ ክልሎች ግመሎችን ስገል የቆዬ ስሆን ችግሩ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆነ የምስራቅ አፍርካም ችግር ነወ።

ይህን ችግር ለመቅረፍ የግብርና ሚኒስቴር በጠየቀው ትብብርና ድጋፍ መሰረት የዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅት (WOAH) ለግመል በሽታ የትብብር ማዕከል የሆነው የአቡዳቢ ግብርናና ምግብ ደህንነት ባለስልጣን (ADFSA) የበሽታውን ናሙና ለመውሰድ ባለፈው ሀምሌ ወር 2016 ዓ.ም መጥተዉ ነበር፡፡

በዚህም የትብብር ማዕከሉ (ADFSA) የተለያዩ የናሙና ዓይነቶችን ሰብስቦ የላብራቶሪ ምርመራውን ያካሄደ ሲሆን የቬሰልስብሮን ቫይረስን (Wesselsbron virus) የለየበት  ውጤቱን በ26ኛው የዓለም አቀፍ እንስሳት ጤና ድርጅት(WOAH) የአፍሪካ አህጉራዊ ጉባኤ ላይ አቅርቧል። ይህን ተከትሎ የኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር እና የአቡዳቢ ግብርና እና ምግብ ደህንነት ባለስልጣን የቬሰልስብሮን ቫይረስ(Wesselsbron virus) ሊፈጥር የሚችለውን ጉዳት እና በኢትዮጵያም ሆነ በምስራቅ አፍሪካ ለግመል ሞት ከሆኑት ምክንያቶች ጋር ያለውን ግንኙነት ለመፈተሽ ለተጨማሪ ጥናትና ምርምር ትብብርን እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።

ያልታወቀ የግመል በሽታ መንስኤ ተብሎ የተገለጸውን ቫይረስ የበሽታው መንስኤ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል በሚለው ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ ሌሎች የበሽታው መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉትን ከግምት ውስጥ በማስገባት የልማት አጋሮች እና በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ባለድርሻ አካላት (FAO፣ IGAD፣ AU-IBAR፣ ILRI፣ AU- PANVAC፣ WOAH የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ተወካይ፣ የአካዳሚክ ፕሮፈሰሮች፣ ዋና የእንስሳት ህክምና መኮንን (CVO) ወይም ተወካዮች (የደቡብ ሱዳን፣ የኬንያ፣ የሶማሌ እና የኢትዮጵያ) እና ሌሎች በእንስሳት ጤና ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል። በዚህም ያልታወቀ የግመሎች በሽታን (UCD)” ለማስቆም ተባብሮ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡ በስምምነቱም፡-

  1. በክልሉ ውስጥ የበሽታውን ዳሰሳና ቅኝት በማጠናከር ቫይረሱን ለመለየት የ ELISA ፀረ እንግዳ አካላትን (Antibody) ማዳበር፤
  2. ከመስክ ላይ ዳግም ናሙና በመሰብሰብ ቀደም ሲል ከታመሙ ግመሎች የተገኘዉን ቫይረስ በላቦራቶሪ መለየት፤
  3. በክልሉ ሪፖርት ለተደረገው ለአልታወቀ የግመል በሽታ ብቸኛ መንስኤ ሆኖ የተገኘውን ቫይረስ እንደገና ለማባዛት በጤናማ ግመሎች ላይ የተለየውን ቫይረስ በመጠቀም ሙከራዎችን ማካሄድ፤
  4. ተለይቶ የታወቀው ቫይረስ ለአልታወቀ የግመል በሽታ መንስኤ እንደሆነ ከተረጋገጠ በሽታውን ለመከላከል የሚያግዝ ክትባት ማበልፀግና ማምረትን መደገፍ፤
  5. በክልሉ እስካሁን ሪፖርት የተደረገው የግመሎች ሞት ምክንያት የሆነው የተለያዩ መሆናቸዉ የምያሳየዉ ምልክት የተለያየ መሆኑ ስለሚለያዩ እና መንስዔያቸዉ የተለያዩ ልሆኑ ስለሚችሉ ለሌሎች የአልታወቀ የግመሎች በሽታ መንስኤዎች ቀጣይነት ያለው ምርመራና ምርምር ስራዎችን  ለመደገፍ ተስማምተዋል።

የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በድርጊት መርሃ ግብር ውስጥ የሚካተቱ ቦታዎችን ጨምሮ ድጋፍ የሚሰጡባቸውን ቦታዎች ለመጠቆም ስለሚያስችሉ በADAFSA በተቀረፀው የድርጊት መርሃ ግብር ስምምነት ላይ ተደርሷል። የኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴር እና የ ADAFSA ፍሬያማ ትብብር አካል የሆነው በክልሉ ግመሎችን የመታደግ ጠቃሚ ተልዕኮ የረጅሙ ጉዞ ጅማሪ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *