FDRE Ministry of Agriculture

በ2018 በጀት ዓመት በግብርና ሚኒስቴር የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞች የዕውቅናና የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ

ቢሾፍቱ፣ ነሐሴ 27/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) ግብርና ሚኒስቴር በ2018 በጀት ዓመት በስራቸው ላቅ ያለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ግምባር-ቀደም ስራ አስፈፃሚዎች፣ ዴስክ ሃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎች እንዲሁም ለባለሙያዎች የዕውቅናና የምስጋና ፕሮግራም አካሂዷል።

በዕለቱ በተካሄደው የዕውቅና እና የምስጋና ስነ-ስርዓት ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል እና የተጠሪ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ግምባር-ቀደም ሰራተኞች የገንዘብ እና የሰርተፊኬት እንዲሁም ሌሎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ይህ የምስጋና እና ዕውቅና ፕሮግራም ሰራተኞች ለበለጠ ስራና ውጤት እንዲነሳሱ ከማድረጉም በላይ፣ በተቋሙ ውስጥ የውድድር እና የበጎ ስራ ባህልን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው በመድረኩ ላይ ተገልጿል።