(አዳማ፣ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)
የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስር ያሉ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች እንዲሁም የክልሎች ህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን የበጀት ዓመቱ የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የሚኒስትሩ ፅ/ቤት ኃላፊ ግርማ በቀለ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙንኬሽን ባለሙያው በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችን ብቻ ሳይሆን ክፍተቶች ላይም በመዘገብ አመራሩ መፍትሄ እንዲያበጅ ማድረግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙንኬሽን ስራ አስፈፃሚ ከበደ ላቀው መንግስት ለግብርናው ዘርፍ ትኩረት በመስጠቱ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ጠቅሰው የተመዘገቡ ውጤቶችን በአግባቡ ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ ህዝብን ለበለጠ ስራ ማነሳሳት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ስራ አስፈፃሚው አክለውም የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ስራን በማጠናከር ምርጥ ተሞክሮዎች በብዛት እና በጥራት ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስር ያሉ ፕሮግራሞች እንዲሁም የክልሎች ህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን የበጀት ዓመቱ የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
ዘጋቢ፡- ዮሐንስ ደመቀ
ፎቶግራፍ፡- ያሬድ አሰፋ