አዲስ አበባ፣ መስከረም 12/2019 (ግብርና ሚኒስቴር) በዘንድሮ የመኸር እርሻ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአጠቃላይ 22 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት በማልማት 730 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዷል፡፡

በዚህም እስካሁን ባለው የእርሻ እንቅስቃሴ በአጠቃላይ 21 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት ታርሶ 19 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ በዘር ተሸፍኗል።
በዘንድሮ የመኸር ወቅት በዋና ዋና ሰብሎች 20 ነጥብ 9 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እስካሁን 17 ነጥብ 9 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ በዘር ተሸፍኗል፡፡

በዋና ዋና ሰብሎች በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ 14 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እስካሁን 11 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለምቷል።
