FDRE Ministry of Agriculture

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የተከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8/2019 (ግብርና ሚኒስቴር) የአለም ባንክ እና የልማት አጋር አካላት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ በመገኘት በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኘ።

ቡድኑ የመስክ ምልከታ ያደረገው የኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም 6ኛ የጋራ ግምገማ እና የትግበራ ድጋፍ ተልዕኮን መነሻ በማድረግ ነው።

በዚህም ቡድኑ በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች በፕሮግራሙ የተገነቡ እና በመገንባት ላይ ያሉ በርካታ ፕሮጀክቶችን ተመልክቷል።

የአነስተኛ አርሶ አደሮች ምርት በቀላሉ ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ የሚያስችል የተገነባ የገበያ ማዕከል፣ የአርሶ አደሩን ምርት ወደ ገበያ የማጓጓዝ ችግር የፈታ አዲስ የተገነባ ድልድይ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘና እየተከናወነ የሚገኝ የመስኖ ፕሮጀክት፣ የቡና ችግኝ ጣቢያ እንዲሁም በቡና ልማት ኢኒሼቲቭ እየለማ የሚገኝ ሰፊ የቡና ልማት ክላስተር ተጎብኝቷል።

በመስክ ምልከታው ከአለም ባንክ እና ከሌሎች የልማት አጋር አካላት በተጨማሪ የግብርና ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች፣ የጉራጌ ዞንና የቸሃ ወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።