FDRE Ministry of Agriculture

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በድሬዳዋ የግብርና ልማት ስራዎችን ጎበኙ

ድሬዳዋ፣ ግንቦት 9/2018 (ግብርና ሚኒስቴር) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ እንዲሁም ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎች በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የግብርና ልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም በዋናነት በሌማት ትሩፋት የተከናወኑ የዶሮ ብዜት ማዕከልና ርባታ፣ የወተት ላሞች እርባታ፣ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም የችግኝ ጣቢያዎች ቅድመ ዝግጅት፣ የብርቱካን ክላስተር እንዲሁም በግሉ ዘርፍ በግብርና ስራ የተሰማሩ ባለሃብቶችና ዩኒየኖች የተሰሩ የልማት ስራዎች ተጎብኝተዋል።

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ ትልቅ ዕድል የሚፈጥሩ መሆናቸው በመስክ ምልከታው ወቅት ተመላክቷል።

ዘጋቢ፦ ሰለሞን ደምሰው

ፎቶ፦ ተክለመድህን አቻምየለህ