FDRE Ministry of Agriculture

ለንቦች ምቹ ስነ-ምህዳር በመፍጠር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል

(ጅማ፣ ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)

ዓለም አቀፍ የንብ ቀን እና 2ኛው ዘላቂ የንብ ማነብና እጽዋት ተራክቦ ጉባኤ በጅማ ከተማ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ጋር በመተባበር ያዘጋጀችው ሁነት አካል የሆነው የምርጥ ተሞክሮ መስክ ምልከታ በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን ማና ወረዳ ተካሂዷል፡፡

በመስክ ምልከታው በማር ምርት ምርጥ ተሞክሮዎች፣ የአቦካዶ ተክሎች፣ የቡና ችግኝ ማባዣ ጣቢያ፣ የዶሮ እርባታ ማዕከል የተጎበኙ ሲሆን የሻይ ቅጠል ችግኝ ተከላም ተካሂዷል፡፡

በመስክ ምልከታው በማር ምርት ምርጥ ተሞክሮዎች፣ የአቦካዶ ተክሎች፣ የቡና ችግኝ ማባዣ ጣቢያ፣ የዶሮ እርባታ ማዕከል የተጎበኙ ሲሆን የሻይ ቅጠል ችግኝ ተከላም ተካሂዷል፡፡

የመስኩ ተሳታፊዎች በወረዳው በንብ ሃብት ላይ የተሰሩ ስራዎችን አድንቀው መንግስት ለዘርፉ ምን ያህል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ዮሐንስ ደመቀ

ፎቶግራፍ፡- ዮዲት እንዳለው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *