ራዕይ፣ተልዕኮና እሴቶች
ራዕይ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ2012 ዓ.ም ተደራሽነት ያለው ሕግ በማውጣትና በማስተግበር ተምሳሌት ከሆኑ አስር የዓለም የከተማ ምክር ቤቶች አንዱ መሆን@
ተልዕኮ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመልካም አስተዳደር፣የልማት፣የዲሞክራስያዊ ስርዓት ግንባታን የሚያረጋግጡ ከተማ አቀፍ ህጎችን ህዝቡን አሳተፎ ማውጣት፤ አስፈጻሚ አካላትን በመከታተልና በመቆጣጠር ፣የም/ቤቱን እንቅስቃሴዎችና ውሳኔዎች በማሳወቅ የከተማውን ነዋሪ ተጠቃሚ ማድረግ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት እሴቶች
- የሕዝቡን ውክልና እናረጋግጣለን
- በእምነትና በእውቀት እንመራለን
- በምክር ቤቱ የዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲረጋገጡ በትጋት እንሰራለን
- በምክር ቤቱ የመቻቻል ባሕልን እናዳብራለን
- ኪራይ ሰብሳቢነትን እንታገላለን
- ሕዝቡን በታማኝነትና በቅንነት እናገለግላለን
- ለሕዝብ ተጠቃሚነት ተግተን እንሰራለን
- የሕግ የበላይነትን እናረጋግጣለን፡፡